assign
assign () መደበ / ተመደበ
- He assigned two men to guard the prisoner.
- እስረኛውን እንዲጠብቁ ሁለት ሰዎች መደበ
- These rooms have been assigned to us.
- እነዚህ ክፍሎች ለኛ ተመድበዋል
assign () ወሰነ / ተወሰነ
- Has a day been assigned for the trial?
- ጉዳዩ በፍርድ ቤት የሚታይበት ቀን ተወስኗል?
assign () ደለደለ
- They assigned all the new children to various classes.
- አዳዲሶቹን ልጆች ልዩ ልዩ ክፍሎች ውስጥ ደለደሏቸው
assign () እንዲያዘጋጅ አዘዘው
- The teacher assigned us two lesson for Monday.
- አስተማሪው ለሰኞ ሁለት ትምህርት እንድናዘጋጅ አዘዘን
assign () አዛወረ
- Mr. Jones assigned his home and farm to his creditors.
- ሚስተር ጆንስ ቤቱን እና እርሻውን ለአበዳሪዎቹ አዛወረ
assign () ሰጠ / ተሰጠ
- He performed the task assigned him with diligence.
- የተሰጠውን ሥራ በትጋት ፈጸመ